ሰበር ‼️
ESCFE 2024
Gent – Belgium
ውድ የፌዴሬሽኛችን ወዳጆች እና አባል ቡድኖች በቅድሚያ በተለያዩ ምክንያቶች የ2024 ዓመታዊ ፌስቲቫል የሚዘጋጅበትን ከተማ ሳንገልፅ በመቆየታችን ለተፈጠረባችሁ ቅሬታ በስራ አመራሩ ስም ከፍ ያለ ይቅርታ መጠየቅ እንወዳለን ።
የ2024 ESCFE በቤልጅየሟ ውብ ከተማ ጌንት ላይ ሆቴል ኮንሰርቶች እንዲሁም የተለያዩ የምሽት ፕሮግራሞች እየተዘጋጁ ሲሆን
Ronse ከተማ በሚገኘው የፌስቲቫሉን ደረጃ በሚመጥን እና ዝግጅቱ የሚፈልጋቸውን አቅርቦቶች የበሚያሙዋላው ግዙፉ የከተማዋ ስታድየም ውስጥ የሚደረግ ይሆናል ።
ከ Gent ወደ Ronse የግማሽ ሰዓት የመኪና ጉዞ ሲሆን በባቡርም መሄድ ይቻላል ።
ተጨማሪ ዝግጅታችንን መሰረት ያደረገ ከ Gent ወደ Ronse የባቡር እና የባስ አማራጮችን አቅርቦት እንዲኖሩ ፌዴሬሽናችን ሀላፊነት ወስዶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል ።
በቂ የሆነ የፓርኪንግ አቅርቦት ስላለን በመኪና እና በባስ ወደ ቤልጅየም የምትመጡ እንግዶቻችን ትበረታታላችሁ 🚘🚌 👌
GENT2024 ኢትዮጵያዊነት ይደምቃል ‼️
ESCFE