18th ESCFE Tournament is Ongoing
LATEST NEWS

ከሁሉ አስቀድመን የማክበር ሰላምታችንን እናቀርባለን። ለተወደዳችሁ በአውሮፓ የባሕል እና ስፖርት ፌዴሬሽን አባላት በሙሉ። በሥራ አመራሩ ስም የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን። ፌዴሬሽናችን ለቡድኖች የትጥቅ ችግር ለመቅረፍ ከሃገር በቀሉ ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የሁለት ዓመት የስፖርት ትጥቅ አቅርቦት የስፖንሰርሽፕ ስምምነት አድርገናል። ይህ ኢትዮጵያዊ የስፖርት አልባሳት ብራንድ ጎፈሬ በዋናናት በአገራችን በተለያዩ ሊግ ለሚሳተፉ ቡድኖች እንዲሁም በምሥራቅ አፍሪካ የትጥቅ…

ፌዴሬሽናችን አምስተዳም ላይ ከ26–29 ጁላይ 2023 በሚደረገው 18ኛው የESCFE ፌስቲቫል ላይ በዓለም አቀፍ ውድድሮች የሀገራችንን ስም በተደጋጋሚ ከፍ አድርጎ ያስጠራው ኢንተርናችናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማን በክብር እንግድነት ሲጋብዝ ትልቅ ኩራት ይሰማዋል ። በዓምላክ ተሰማ በቅርቡ በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜን ውድድር እንዲመራ የተመረጠ ሲሆን ፌዴሬሽናችንም የዓመታዊ ውድድር መዝጊያ የሆነውን የፍፃሜ ጨዋታ አልቢትር በአምላክ እንደሚመራው ስንገልፅ ከወዲሁ…
First Day Amsterdam 2023
አምስተርዳም ላይ 18ኛው ESCFE ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊነትን ባደመቀ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል ።
በፕሮግራማችን ላይ የክብር እንግዶቻችንን ኢተርናሽናል ዳኛን በአምላክ ተሰማን እና የቀድሞ ተጫዋች አካለወርቅ ሳልልህ (አክሻ) የሚገባቸውን ክብር ሰጥተን ፕሮግራማችንን ከፍተናል።