
ሉቻኖ ቫሳሎ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ታሪክ የነበረው ለረጅም ዓመታት የሀገሩን ሰንደቅ ከፍ ያረገ አይረሴ ተጫዋች ነው ። ፌዴሬሽናችን በ2008 ስውዲን ስቶኮልም አዘጋጅቶት በነበረው የ6ኛው ESCFE ላይ ከሌላኛው ባለታሪክ መንግስቱ ወርቁ ጋር የክብር እንግዳ እንደነበር እና ፌዴሬሽናችንም በሚገባው ልክ ባይሆንም ትልቅ አክብሮቱን ገልፆለት እንደነበር የሚታወስ ነው ። ESCFE ባለፈው ዓመት በድንገት ያጣነውን ይህን…