ፌዴሬሽናችን አምስተዳም ላይ ከ26–29 ጁላይ 2023 በሚደረገው 18ኛው የESCFE ፌስቲቫል ላይ በዓለም አቀፍ ውድድሮች የሀገራችንን ስም በተደጋጋሚ ከፍ አድርጎ ያስጠራው ኢንተርናችናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማን በክብር እንግድነት ሲጋብዝ ትልቅ ኩራት ይሰማዋል ።

በዓምላክ ተሰማ በቅርቡ በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜን ውድድር እንዲመራ የተመረጠ ሲሆን ፌዴሬሽናችንም የዓመታዊ ውድድር መዝጊያ የሆነውን የፍፃሜ ጨዋታ አልቢትር በአምላክ እንደሚመራው ስንገልፅ ከወዲሁ ደስታም ክብርም እየተሰማን ነው ።