ESCFE በቀን 26/10/2024 በፍራንክፈርት ከተማ 19ኛውን የፌዴሬሽኑን ጠቅላላ ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ አካሂዶዋል ።
የፌዴሬሽኑ የቦርድ አባላት በ19ኛው የቤልጅየም ዝግጅት ሂደት እና ክንውን ላይ በቀረበው ሪፖርት እና በእለቱ ከቤቱ በተነሱት ተጨማሪ አጀንዳዎች ላይ ጥልቅ ውይይት እና ግምገማ ያደረጉ ሲሆን በተለይ የስራ ግዜውን አጠናቆ በነበረው ነባሩ የስራ ዓመራር አተካክ ላይ ከስነስርዓት እና ሕጋዊነት ዙርያ ሰፋ ያሉ ውይይቶች ተደርገው ቤቱ የጋራ መግባባት ላይ ደርሶ ውሳኔውን አስተላልፎዋል ።
በጉባዔውም ነባሩ የስራ ዓመራር በቀጣይ 20ኛው ዓመት የፌዴሬሽኑ ዝግጅት ደረጃውን ጠብቆ ይዘጋጅ ዘንድ ጠንከር ያለ አቅምና ዝግጅት ስለሚያስፈልግ ሙሉ ለሙሉ የስራ ዓመራሩ ለአንድ ዓመት የስራ ግዜው እንዲራዘም እና አራት አዳዲስ አመራሮች በተጨማሪነት ለአንድ አመት ነባሩን የስራ ዓመራር እንዲቀላቀሉ ወስኖዋል ።
ውሳኔውን ተከትሎም የቦርድ አባላት ተወካዮች ስድስት እጩዎችን በጥቆማ ያቀረቡ ሲሆን ከስድስቱ ሶስቱ አብላጫውን ድምፅ በማግኘት እንዲሁም ቤቱ ሴት እህቶቻችን ወደ ስራ አመራሩ ቢቀላቀሉ አበረታች ነው የሚል እምነት በመያዙ አንድ እህታችንን በቀጥታ በማሳለፍ ባጠቃላይ አራት አዳዲስ አባላት ወደ ፌዴሬሽናችን የስራ ዓመራርነት እንዲመጡ በመምረጥ 19ኛውን ዓመታዊ የጠቅላላ ጉባዔ አጠናቆዋል ።
ወ/ሮ ስርጉት ተካ
አቶ ባዩ ሙሉ
አቶ ገነነ መክብብ
አቶ ፊሊሞን በላይ
እንኳን ወደ ESCFE ስራ ዓመራርነት በሰላም ተቀላቀላቹ እያልን የስራ ዘመናቹ የስኬት እንዲሁም የምትወዱትን ፌዴሬሽን የምታገለግሉበት ለለውጡ የምትተጉበት እንዲሆን እንመኛለን ።
source : https://www.facebook.com/escfe