ከሁሉ አስቀድመን የማክበር ሰላምታችንን እናቅርባለን። በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን አመራሩ ስም የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን። በተለያዩ መንገዶች እንደሰማችሁት የዚህ ዓመት ዝግጅት ከሶስት ዓመት በሆላ ከ26.07.2023 እስከ 29.07.2023 በአምስተርዳም እንደሚዘጋጅ አሳውቀናል። የዘንድሮው ዝግጅት በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ሙሉ ሃላፊነት እንደሚዛጋጅ ላልሰማችሁ በዚህ መንገድ ማሳወቅ እንወዳለን። ሆኖም ይህ ዝግጅት እስከዛሬ ሲዘጋጅ በየዝግጅቱ ወቅት እንከን እንደማያጣው ያለፉት 17 ዝግጅቶች አሳይቶል። የነዚህ ችግሮች ዋነኛዉ መክንያትም ዝግጅቶቹ ሲዘጋጁባቸው የነብሩበት አካሄድ በባለሙያ አለመዛጋጀታቸውና የስራው ጫና አዘጋጆቹ ላይ በመብዛቱ ስህተቶች ይበዙና ዝግጅቱ ወደ አልተፈለገበት መንገድ ሲሄድ ይታወሳል። ሆኖም አሁን ፌዴሬሽኑ ይህንን ለመቅረፍ በባህል ስራ ላይ ከመክፈቻው ከዕሮብ ጀምሮ እስከ መዝጊያው ዝግጅት ቅዳሜ ማታ፣ ቀን በኳስ ሜዳዉም ይሁን ማታ በተለያዩ አዳራሾች ከባለሙያዎች ጋር አብሮ ለመስራት በዚህ መንገድ ጥሪዉን ያቀርባል። በባህል ዙሪያ የምትሰሩ ሃሳብችሁን በፌዴሬሽኑ ኢሜል እንድታሳዉቁን እንወዳለን እና መሳተፍ የሚፈልጉትን ቦታና ስራ አይተን የ zoom ውይይት አድርገን ዝግጅቱን ለማሳመር ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪዉን ያቀርባል። 1. በኳስ ሜዳ የተለያዩ የባህል *ሙዚቃዎች እንዲሁም ፋሽን ሾው ትሪኢቶች የምታቀርቡ2. በኳስ ሜዳ ለልጆች ወይንም ለአዋቂዎች ባህላዊ ይሁን ትምህርት ሰጪ ጨዋታዎችን ማቅረብ ለምትፈልጉ3. በኳስ ሜዳ የስነ ጽሁፍ ግጥሞች ቲያትሮች ማቅረብ የምትፈልጉ4. ከእሮብ ማታ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ማታ በአዳራሽ የሙዚቃ የቲያትር እንዲሁም ፋሽን ሾው ዝግጅቶችን ማቅረብ ለምትፈልጉ በሙሉ ፌዴሬሽኑ ያቀረበዉን አብሮ የመስራት ፍላጎትን ተቀብላችሁ በአውሮፓ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከዘረ፣ ከሃይማኖት፣ ከፓለቲካ ነፃ በሆነ መልኩ በአንድ የስፖርትና ባህል ጥላ ስር የሚገናኘበትን መድረክ ለመፍጠር፣ ቤተሰባዊ የሆነ አስተሳሰብ በስፖርትና በባህል እንቅስቃሴ አማካኝነት በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲሰረፅ ማድረግ፣ በስራ የተዳከመ አካልንና በሃሳብ በጭንቀት የተወጠረ አእምሮን በስፖርትና ባህል አማካኝነት ለማዝናናትና ለማደስ፣ በአዉሮፓ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ማሳተፍ የሚችል በእረፍትና አመቸ በሆነ ጊዜ የሚያዝናና ስፖርታዊና ባህላዊ ጨዋታዎችንና ስፍራዎችን ማዘጋጀት፣ ወጣቱንና ጎልማሳዎችን ከአልባሌ ነገሮች ራሳቸዉን ለመከላከል እንዲችሉ መረዳትና የስፖርት እንቅስቃሴዎችን እንዲሳተፋ ማበረታታት የሚል ነው። ዘንድሮ እንደ ጅምር በዚህ መልኩ ጀምረነው ለወደፊቱ ደግሞ እየተለመደና የፌዴሬሽኑ አሰራር ሆኖ እንዲቀጥል በሁላችሁም ድጋፍ ይቀጥላል። ፌዴሬሽኑ ከሶስት ዓመት ኮረና በሆላ ለብዙ ወጭ ተዳርጎል ስለዚህ በዚህ መንገድ መሳተፍ ለምትፈልጉ ወጫችሁን በራሳችሁ ወይንም በማህበራችሁ ድጋፍ መሆን ይጠበቃል። በመጨረሻም ፌዴሬሽኑ ለምታደርጉት መልካም ትብብር የከበረ ምስጋናውን እያቀረበ መልካሙን ሁሉ ይመኝላችዃል። ከስላምታ ጋር፣ ስራ አስኪያጂ ኮሚቴ