
ESCFE ዘንድሮ አምስተርዳም ላይ የሚደረገውን 18ኛውን የስፖርት እና የባሕል ፌስቲቫል የ2ኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ዋንጫ ስያሜ በአንጋፋው የስፖርት ሰው ጋሽ ፍቅሩ ኪዳኔ መታሰቢያ እንዲሆንለት ሲሰይም ክብር ይሰማዋል ። ባለፈው ዓመት ፈረንሳይ ፖሪስ ውስጥ በሞት ያጣነው ጋሽ ፍቅሩ በ2016 ሆላንድ ዴንሃግ ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው የፌዴሬሽናችን 14ኛው ዓመት ESCFE ላይ የክብር እንግዳችን በማድረግ የሚገባውን ክብር የሰጠነው ሲሆን…