ከሁሉ አስቀድመን የማክበር ሰላምታችንን እናቀርባለን።

ለተወደዳችሁ በአውሮፓ የባሕል እና ስፖርት ፌዴሬሽን አባላት በሙሉ። በሥራ አመራሩ ስም የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን።

ፌዴሬሽናችን ለቡድኖች የትጥቅ ችግር ለመቅረፍ ከሃገር በቀሉ ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የሁለት ዓመት የስፖርት ትጥቅ አቅርቦት የስፖንሰርሽፕ ስምምነት አድርገናል። ይህ ኢትዮጵያዊ የስፖርት አልባሳት ብራንድ ጎፈሬ በዋናናት በአገራችን በተለያዩ ሊግ ለሚሳተፉ ቡድኖች እንዲሁም በምሥራቅ አፍሪካ የትጥቅ አቅርቦት በማድረግ የሚታዎቅ ሲሆን አሁን በቅርቡም  ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴርሽን ጋር በተለያዩ የእድሜ እርካን ላይ አገራችንን ወክለው ለሚሳተፉ ቡድኖች የትጥቅ አልባሳትን ለማቅረብ ስምምነት ፈጽሟል።

ከኛ ጋር የተፈጸመውም ስምምነት ለአባል አገራትና ቡድኖች ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለን እናምናለን ይህም ስምምነት የቡድኖችን የትጥቅ ችግር የሚፈታና ይህንን ኢትዮጵያዊ ብራንድ ትጥቅ አምራች ድርጅትም ወደ ዓለም አቀፍ ተዎዳዳሪነት መሸጋጋሪያ መድረክ በመፍጠራችንም ደስተኞች ነን።

  • ጎፈሬ በስምምነቱ  የ50% ቅነሽ በማድረግ ለቡድኖች ትጥቅ ያቀርባል
  • ጎፈሬ  በስፖንሰር በጥራት በፍጠነት ለፌዴሬሽኑ ያቀርበል
  • በዓመታዊ በውድድሩ ለሚገኙ ቡድኖች በአስፈላጊ ወቅትና ጊዜ ትጥቆችን በጥራት በብዛትና እንዲሁም ዲዛይን በፍጥነት ያቀርባል

ከጎፈሬ ጋር በትጥቅ አቅርቦትና በጋራ በሚያሰሩን ሥራዎች በመመካከር በመደጋገፍ እንዲሁም ሁለቱንም ተቋማት ተጠቃሚ በሚያደርጉ ጉዳዮች ጋር በጋራ ይሰራሉ። ቡድኖችም የ50% ቅናሽ ተጠቃሚ ለመሆን ትጥቅ ማዘዝ ከፈለጉ ፌደሬ ሽኑን ግኑኝነት በማድረግ የቅናሽ ማዘዣ የሚስጢር ኮድ በመቀበል መፈጸም ይችላሉ በምትፈልጉት ዓይነት ዲዛይን ላማሰራት በትንሹ የ4ሳምንት ጊዜ ስለሚያስፈልግ ፍላጎቱ ያላቹ ቀደም ብሎ ትዕዛዝ መፈጸሙ ይመከራል ለዚሁም የፌደርሽናችንን ም/ፕሬዝዳንት ሮቤርቶ ካንቲን  በስልክ ቁጥር 00393479110083 በመደወል መፈጸም ይችላሉ። በመጨረሻም ፌዴሬሽኑ ለምታደርጉት መልካም ትብብር የከበረ ምስጋናውን እያቀረበ መልካሙን ሁሉ ይመኝላችዃል።

ከሰላምታ ጋር

በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን

የጎፈሬን ካታሎግ ይህን ሊንክ በመጫን ያግኙት