ውድ እና የተከበራችሁ የፌዴሬሽናችን ወዳጆች አምስተርዳም ከተማ ከ26 – 29 July 2023 በሚደረገው 18ኛው የ????? ፌስቲቫል ለመሳተፍ ወስናችሁ ሆቴል እና መሰል ተያያዥ ነገሮችን ለማመቻቸት በተደጋጋሚ የዝግጅቱን ቦታ አድራሻ እየጠየቃችሁን የነበረ ሲሆን እኛም ተገቢውን ምላሽ በግዜው ልንሰጣችሁ ባለመቻላችን ለተፈጠረባችሁ ቅሬታ በፌዴሬሽኑ ስራ አመራር ስም ከልብ ይቅርታችሁን እንጠይቃለን ።

የዝግጅቱን ቦታ ለዝግጅቱ ታዳሚያን ለማሳወቅ ከቦታው አስተዳዳሪዎች እና ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር ሕጋዊ በሆነ መልኩ መጨረስ የነበሩብን ጉዳዩች በወቅቱ ማለቅ ባለመቻላቸው አድራሻውን ለመግለፅ አዘግይቶን የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ሁሉም በታቀደለት መልኩ እየሄደ ስለሆነ ውድ የዝግጅታችን ናፋቂዎች የጉዞ እና የሆቴል ጉዳዮቻችሁን ከወዲሁ እንድትጨርሱ እናበረታታለን ።

 

???? ??????? ?, 1097 HK Amsterdam, Netherlands