በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን የባሕል እና የስፖርት ፌስቲቫል ከ July26 – 29 July 2023 አምስተርዳም (ሆላንድ) ይካሄዳል።
ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ የሚካሄደውን የስፖርት ፌስቲቫልን አስመልክቶ ትላንት የማህበሩ አባላት እና የቡድን ተወካዮች በተገኙበት ፌስቲቫሉ የሚዘጋጅበትን የሜዳ ጉብኝት እና የፌዴሬሽኑን ያለፉ እንዲሁም ቀጣይ ዕቅዶች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በተጨማሪም ዘንድሮ በሚያካሂደው አመታዊ ፌስቲቫል ላይ 39 ቡድኖች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ሲገለፅ የአንደኛ እና የሁለተኛ ዲቪዚዮን የምድብ ድልድል ይፋም ተደረጓል።

በተያያዘ 2023 አምስተርዳም (ሆላንድ) ላይ በሚያካሂደው አመታዊ ፌስቲቫል ላይ ለንግድ እና ለማስታወቂያ አገልግሎት ፈላጊዎች የድንኳን ኪራይ ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።
በዚህ ዓመታዊ ዝግጅት ላይ ድንኳን በመከራየት ልዩ ልዩ ስራዎችን መስራት ለሚፈልጉ ሁሉ ፌዴሬሽኑ እንዲያናግሩ ጥሪውን አስተላልፏል።