ESCFE ዘንድሮ አምስተርዳም ላይ የሚደረገውን 18ኛውን የስፖርት እና የባሕል ፌስቲቫል የ2ኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ዋንጫ ስያሜ በአንጋፋው የስፖርት ሰው ጋሽ ፍቅሩ ኪዳኔ መታሰቢያ እንዲሆንለት ሲሰይም ክብር ይሰማዋል ።
ባለፈው ዓመት ፈረንሳይ ፖሪስ ውስጥ በሞት ያጣነው ጋሽ ፍቅሩ በ2016 ሆላንድ ዴንሃግ ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው የፌዴሬሽናችን 14ኛው ዓመት ESCFE ላይ የክብር እንግዳችን በማድረግ የሚገባውን ክብር የሰጠነው ሲሆን አሁን ደግሞ ለሰራው ዘመን ተሻጋሪ ስራ ክብር እንዳለን ለማሳየት የዘንድሮን የሁለተኛ ዲቪዚዮን ዋንጫ በስሙ ሰይመንለታል ።
ጋሽ ፍቅሩ ኪዳኔ አንጋፍ የስፖርት ጋዜጠኛ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሸን ሊቀመንበር እንዲሁም የካፍ እና የኢተርናሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራር በመሆን ያገለገለ በዓለም ስፖርት ቤተሰብ ዘንድ ትልቅ ስም እና ክብር የነበረው ኢትዮጵያዊ ነው ።
የፒያሳው ልጅ ጋሽ ፍቅሩ መቼም አንረሳህም