Great news
  1. Art Exhibition and Kids Workshop by Artist Painter Haimi Art
  2. Legend Footballer Zelalem Teshome
  3. LEGEND FOOTBALLER ASEGED TESFAYE
  4. ሮማ ታሪካዊ ከተማ፤ መጠንቀቅ እንጂ መቆም መፍትሔ አይሆንም፤፤
  5. ESCFE RADIO Program 29.01.2017 | 19 – 21 H

Kids

ልጆች
ስፖርት በልጆች በተለይም በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ያለው ተፅዕኖ፤

እንደ ሳይንስና የፈጠራ ምርምሮች መረጃዎች የሰው ልጅን አፈጣጠርና አመጣጥ ከሃይማኖታዊ አገላለፅና አመለካከት የተለየና ተፃራሪ ቢሆንም ተቀባይነቱ አናሳ ሆኖ ይታያል። የሆነው ሆኖ ምርጫ የራስ ነውና ወደ አብዛኛው እናዘንብልና “እግዚአብሔር ሰውን በራሱ አምሳል ፈጠረው፤ በምድርም ላይም ብዙ ተባዙም አለ።” ይህም የእግዚአብሔር ቃልም እውን ሆነ፤ የሰው ልጅም መባዛት ጀመረ ፤ ምትኩን ወደ ምንኖርባት ምድር ማምጣት ቻለ።

ልጆች ማለት ምትክ ማለት ናቸው፤ ልጆች የቤተሰብ በረከቶች ማለት ናቸው፤ በመልካም አስተሳሰብ የተቀረፁ ልጆች አድማሰ ሰፊና የመልካም ስራ ውጤቶች ምሳሌ ሆነው ያድጋሉ። ይህም ማለት ሚዛናዊ፣ጎጂና ጠቃሚውን ለይተው ከመረዳት ባሻገር አልፈው ተርፈውም ለህብረተሰባቸው ዕድገት ትልቅ አሴቶች ይሆናሉ። ለአገርና ለወገኑም ኩራት ይሆናልና መንከባከብ፣ ብሎም በመልካም አስተሳሰብ ታንፀው እንዲያድጉ ግድ ይላል። ይህንንም ጤናማና መልካም አስተሳሰብን ከራስ አልፎ ለሌሎች አሳቢና ተቆርቋሪ ትውልድን ለማዘጋጀት መሰረት ለማጣል ይቻል ዘንድ ሰዎች በመቻቻልና ልዩነታችን እንዳለ ሆኖ ወይንም በማጥበብ ለጋራችን ራዕይ በጋራ መጓዝና መስራት ይጠበቅብናል። ይህንን በማድረግ ያልተበረዘ፣ ነፃ አስተሳሰብና አመለካከት የተላበሰ ትውልድን ማፍራት ብሎም ማዘጋጀት ይቻላል። ስፖርትም በዚህ ረገድ እየተጫወተው ያለው ሚና ከፍተኛ ሆኖም ይገኛል።

በአውሮፓ የኢትዮጲያውያን ስፖርትና የባህል ፌድሬሽንም የነገን የኢትዮጲያ ልጆች በመልካም አስተሳሰብ የታነፁ፣ ነፃ አመለካከት ያላቸው ሆነው እንዲያድጉ የሚደረግን ጥረት ሆሌም የሚደግፍና ወደፊትም ህብረተሰባችን በተለይም ልጆች፣ ወጣቶች በስፖርት ስነ ስርዓት የታነፁ ብሎም ከመጥፎና ጎጂነት ካላቸው ነገሮች ራሳቸውን መከላከል እንዲችሉና በዚሁም ስብስብ አኳያም ስለ አገራቸው ባህልና የአኗኗር ዘዬን ሊማሩበት የሚችሉበትን መድረክ ለማመቻቸት የበለጠ በመስራት ላይም ይገኛል።

ልጆች፤

የዛሬ አበባዎች የነገው ፍሬዎች፣

ከእኛው የወጡ የእኛው አብራኮች፣

ከእግዜር የተሰጡን ታላቅ በረከቶች፣

የእኛው መገለጫ ደግሞም መተኪያዎች፣

መጠሪያዎቻችን መኩሪያና ተስፋዎች፣

የነገውን ተስፋ አንፀባራቂዎች፣

ከእኛው አልፈው ተርፈው የአገር መመኪያዎች፣

በእውነት ፍቅር ናቸው ስላም መልዕክተኞች።

ልጆች ይኮትኮቱ በመልካም ምግባሮች፣

ሆነው እንዲያድጉ መልካም አሳቢዎች፣

ልጆች ይታገዙ ለመልካም ተግባሮች፣

ሆነው እንዲያድጉ አርቆ አሳቢዎች፣

ልጆች ይታገዙ ለመልካም ስራዎች፣

ሆነው እንዲያድጉ የአገር አሰቶች።

ስፖርት ነፃ መድረክ መልካም ነው ምሳሌ፣

በአንድ ላይ አዋለ ጌቶችን ከሎሌ፣

ስፖርት መልካም ባህል የሰላም ውጤት፣

በቡድን ተናጠል አቅም በቻለበት፣

ሁሉን የሚያሳትፍ በአለው ልዩነት፣

የራስ ጥንካሬ የሚፈተንበት፣

መገናኛ መድረክ አህጉር ከአህጉራት

ስፖርት ሆኖ ይገኛል የጋራችን ቤት።