የ #ESCFE መግለጫ ዶ/ር አብይ አሕመድን በተመለከተ
………………………………………………………………….

ቀን 31.05.2018

ለሚመለከተው ሁሉ !

በቅድሚያ ሰላምታችንን እናቀርባለን,

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድን የሰሜን አሜሪካ የስፓርት ፌስቲቫል ዝግጅት ላይ መገኘት መፈለግን አስመልክቶ ባለፋት ጥቂት ቀናት በተለያዩ ሜዲያ ተቋሞችና የሶሽያል ሜዲያ ድረ ገፆች ላይ በተለቀቁት ዘገባዎች ውስጥ በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን የስፓርትና ባህል ፌዴሬሽንም ተመሳሳይ ጥያቄ እንደተጠየቀና ምላሽ እንደተሰጠበት አስመስለው ያሰራጩ ሜዲያ ተቋሞች መኖራቸውን በመገረም ሰምተናል ፣ አንበናል ።

በመጀመሪያ ነገር በአውሮፓ የኢትዮጵያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ራሱን የቻለ በራሱ መተዳደሪያ ደንብ የሚመራ ፣ የራሱ የረጅም ጊዜ ልምምድ ያላቸው የበሰሉ የቦርድ ዓባላትና የዓመራር አካሎች ያሉት ጠንካራና ነፃ ድርጅት ነው ።

በመሆኑም በሜዲያ እንደተዘገበው የሰሜን አሜሪካውን መልስ ሰምተን መልስ እንሰጣለን አሉ የሚለው አይነት በሬ ወለደ ዓይነት ከእውነት ፈፅሞ የራቀ አሳሳች መልዕክት መሆኑን ስናስታውቅ ያሰራጩትን አካሎች ሳያመሳክሩ ዜናውን በመልቀቃቸው የሚገባቸውን ትልቅ ወቀሳ በማከል ነው።
ለወደፊቱ ሳያጣሩና የሚመለከታቸውን ክፍሎች ሳያነጋግሩ ከእንዲህ አይነት አሳሳች ፣ አወዛጋቢ መልዕክቶች እንዳያሰራጩም አጥብቀን እንመክራለን ።
በመጨረሻም በአውሮፓ የኢትዮጵያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ከ August 1-5. 2018 Stuttgart ( German ) ከተማ ላይ በሚያደርገው ዓመታዊው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ለመገኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ቢሮም ሆነ ከኤምባሲው የደረሰን ምንም ዓይነት ደብዳቤ የፌዴሬሽናችን ፅህፈት ቤት እንዳልደረሰውም ።
በሜዲያ እንደተገለፀውም ስለ ጉዳዩ ከዚህ በፊት አስተያየትም ሆነ ምንም ዓይነት መልስ እንዳልሰጠን ለስፓርት ቤተሰቡም ሆነ ከዛ ውጭ ላሉ ሁሉ በትህትና እስናስታውቃለን ።

ከምስጋና ጋር
በአውሮፓ የኢትዮጵያን ስፖርትና በህል ፌዴሬሽን
የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ