ESCFE ዘንድሮ አምስተርዳም ላይ የሚደረገውን 18ኛውን የስፖርት እና የባሕል ፌስቲቫል የ2ኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ዋንጫ ስያሜ በአንጋፋው የስፖርት ሰው ጋሽ ፍቅሩ ኪዳኔ መታሰቢያ እንዲሆንለት ሲሰይም ክብር ይሰማዋል ። ባለፈው ዓመት ፈረንሳይ ፖሪስ ውስጥ በሞት ያጣነው ጋሽ ፍቅሩ በ2016 ሆላንድ ዴንሃግ ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው የፌዴሬሽናችን 14ኛው ዓመት ESCFE ላይ የክብር እንግዳችን በማድረግ የሚገባውን ክብር የሰጠነው ሲሆን…
የ18ኛው የESCFE ውድድር የክብር እንግዶች በሰላም እየደረሱ ነው
ሉቻኖ ቫሳሎ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ታሪክ የነበረው ለረጅም ዓመታት የሀገሩን ሰንደቅ ከፍ ያረገ አይረሴ ተጫዋች ነው ። ፌዴሬሽናችን በ2008 ስውዲን ስቶኮልም አዘጋጅቶት በነበረው የ6ኛው ESCFE ላይ ከሌላኛው ባለታሪክ መንግስቱ ወርቁ ጋር የክብር እንግዳ እንደነበር እና ፌዴሬሽናችንም በሚገባው ልክ ባይሆንም ትልቅ አክብሮቱን ገልፆለት እንደነበር የሚታወስ ነው ። ESCFE ባለፈው ዓመት በድንገት ያጣነውን ይህን…
በተለያዩ ዓለማት በመዘዋወር በትላልቅ መድረኮች ላይ አስገራሚ ብቃታቸውን ባሳዩ ታዳጊዎች የተዋቀረው የሰርከስ ባሕር ዳር ቡድን 18ኛውን የኢትዮጵያዊያን ስፖርት እና ባሕል ፌዴሬሽን በአውሮፖ ፌስቲቫል ለማድመቅ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል ።
ከሁሉ አስቀድመን የማክበር ሰላምታችንን እናቀርባለን። ለተወደዳችሁ በአውሮፓ የባሕል እና ስፖርት ፌዴሬሽን አባላት በሙሉ። በሥራ አመራሩ ስም የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን። ፌዴሬሽናችን ለቡድኖች የትጥቅ ችግር ለመቅረፍ ከሃገር በቀሉ ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የሁለት ዓመት የስፖርት ትጥቅ አቅርቦት የስፖንሰርሽፕ ስምምነት አድርገናል። ይህ ኢትዮጵያዊ የስፖርት አልባሳት ብራንድ ጎፈሬ በዋናናት በአገራችን በተለያዩ ሊግ ለሚሳተፉ ቡድኖች እንዲሁም በምሥራቅ አፍሪካ የትጥቅ…
ፌዴሬሽናችን አምስተዳም ላይ ከ26–29 ጁላይ 2023 በሚደረገው 18ኛው የESCFE ፌስቲቫል ላይ በዓለም አቀፍ ውድድሮች የሀገራችንን ስም በተደጋጋሚ ከፍ አድርጎ ያስጠራው ኢንተርናችናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማን በክብር እንግድነት ሲጋብዝ ትልቅ ኩራት ይሰማዋል ። በዓምላክ ተሰማ በቅርቡ በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜን ውድድር እንዲመራ የተመረጠ ሲሆን ፌዴሬሽናችንም የዓመታዊ ውድድር መዝጊያ የሆነውን የፍፃሜ ጨዋታ አልቢትር በአምላክ እንደሚመራው ስንገልፅ ከወዲሁ…
ከሁሉ አስቀድመን የማክበር ሰላምታችንን እናቅርባለን። በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን አመራሩ ስም የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን። በተለያዩ መንገዶች እንደሰማችሁት የዚህ ዓመት ዝግጅት ከሶስት ዓመት በሆላ ከ26.07.2023 እስከ 29.07.2023 በአምስተርዳም እንደሚዘጋጅ አሳውቀናል። የዘንድሮው ዝግጅት በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ሙሉ ሃላፊነት እንደሚዛጋጅ ላልሰማችሁ በዚህ መንገድ ማሳወቅ እንወዳለን። ሆኖም ይህ ዝግጅት እስከዛሬ ሲዘጋጅ በየዝግጅቱ ወቅት እንከን እንደማያጣው ያለፉት…
- 1
- 2