#መግለጫ

𝗘𝗦𝗖𝗙𝗘 has decided to Cancel the 18th annual tournament that will be held in Amsterdam 

ውድ በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ባሕል እና ስፖርት ፌዴሬሽን ወዳጅ እና አባላት እንዲሁም በዘንድሮው ዝግጅታችን ለመሳተፍ አቅዳችሁ ለነበራችሁ በሙሉ

ከጁላይ 29 እስከ ኦገስት 01 2020 ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የ18ኛው አመት ዝግጅታችን በአለማችን ብሎም የምንኖርበት አውሮፓ በአሁኑ ግዜ ትልቅ ፈተና እና ስጋት እየሆነ በመጣው የ 𝐂𝐎𝐕𝐈𝐃-𝟏𝟗 ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የፌዴሬሽኑ የስራ አመራር እና በአመስተርዳም የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሜቴ ጠቅላላ የዝግጅቱ የማዘጋጀት ሂደት ላይ ግምገማ እና ውይይቶችን በማድረግ ለጠቅላላ ጉባዬው ያቀረቡ ሲሆን ቤቱም በሙሉ ድምፅ ዝግጅቱ እንዲሰረዝ ወስኖዋል ።

#ማስገንዘብያ ፌዴሬሽናች ባለበት ማህበራዊ ሃላፊነት በ 𝐂𝐎𝐕𝐈𝐃-𝟏𝟗 ምክንያት ከሀገራችን እና ከህዝባችን ጎን መቆምና እና ለወገናችን የመድረስ ግዴታ እንዳለብን ስለምናምን በቀጣይ ቀናት ለወገኖቻችን ለመድረስ እርዳታ የምናሰባስብ እና የምናስተባብር መሆኑን ልንገልፅላችሁ እንወዳለን!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ሕዝቦችዋ ይጠብቅ

18th February 2020
1st February 2020

No news in this category

18th February 2020
1st February 2020